Download this Blogger Template by Clicking Here!

Ad 468 X 60

Saturday 23 August 2014

Widgets

መፀዳዳትና ስርዓቶቹ



መፀዳዳትና ስርዓቶቹ

በውስጡ በርካታ ነጥቦች ተካተዋል

                                        አንደኛ

“ኢስቲንጃእ” እና “ኢስቲጅማር” አንዱ ሌላውን እንደሚተካ

“ኢስቲንጃእ” ማለት የመፀዳጃ አካሎችን በውሃ ማጠብ ሲሆን
“ኢስቲጅማር” ደግሞ በድንጋይና በመሳሰሉ አፅጂ ነገሮች ሀፍረተ ገላን ማፅዳት ነው፡፡
ከሁለቱ አንዱን ብቻ መጠቀም በቂ ነው፡፡ ለዚህም ማስረጃው:-
አነስ ያስተላለፉት ሀዲስ ነው “ነብዩ መፀዳጂያ ቤት ሲገቡ እኔና አንድ ልጅ ውሃ ያለበት እቃና ምርኩዝ እንይዝላቸው ነበር እሳቸውም በውሃ ይፀዳዱ ነበር” (ሙስሊም ዘግበውታል)::

ዓኢሻ ባስተላፉትም ሀዲስ ነብዩ እንዲህ ብለዋል:-
“አንድ ሰው ሲፀዳዳ በሶስት ድንጋይ ያፅዳ ይህ በቂው ነው፡፡” (አህመድ ዘግበውታል)
ሆኖም ግን ሁለቱንም አንድ ላይ መጠቀሙ የተሻለ ነው፡፡

“ኢስቲጅማር” በድንጋይና ድንጋይን ሊተኩ በሚችሉ ነገሮች ለምሳሌ ሶፍት እንጨት በመሳሰሉት መጠቀም ይቻላል፡፡ ምክንያቱም ነብዩ ሲጠቀሙት የነበረው ድንጋይ ቢሆንም መሰል አፅጂ ነገሮችም ተመሳሳይ ናቸው፡፡

የአንድ ሰው ምርጫ ኢስቲጅማር ከሆነ ከሶስት ባነሰ ድንጋይ ሊሆን አይችልም ::
ማስረጃውም ሰልማን እንዳሉት:-

“የአላህ መልዕክተኛ በቀኝ እጅ ኢስቲንጃእ ማድረግ፣ ከሶስት ባነሰ ድንጋይ በእንስሳ እዳሪ ወይም በአጥንት ማፅዳትን ከልክለውናል፡፡” (ሙስሊም ዘግበውታል)

ሁለተኛ

ሲፀዳዱ ወደ ቂብላ መዞር ወይም ለቂብላ ጀርባን መስጠት


ሲፀዳዱ አውላላ ሜዳ ላይ ግርዶሽ ሳይኖር ለቂብ ፊትንም ሆነ ጀርባን መስጠት አይፈቀድም፡፡ ለዚህ ማስረጃ አቡ አዩብ አል አንሳሪ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል
“ ለመፀዳዳት ስትሄዱ ወደ ቂብላ ፊታችሁንም ጀርባችሁንም አትስጡ ነገር ግን ወደ ምስራቅና ምዕራብ ዙሩ” አቡ አዮብ እንዲህ አሉ “ወደ ሻም ስንጓዝ መፀዳጃ ቤቶችን ወደ ቂብላ አቅጣጫ ዞረው የተገነቡ ሆነው አገኘንና ለመፀዳዳት ስንፈልግ ትንሽ ዘንበል ብለን እንፀዳዳና ከዚያ አላህን ምህረት እንጠይቃለን፡”
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)


በክፍል ውስጥ ወይም በሱና በከዕባ መካከል ግርዶሽ ኖሮ የሚፀዳዳ ከሆነ ግን ችግር አይኖረውም፡፡ ለዚህም ማስረጃ ኢብኑ ዑመር እንዲህ ብለዋል:-
“የአላህ መልዕክተኛ ወደ ሻም ዞረው ለከዕባ ጀርባቸውን ሰጥተው ሲፀዳዱ አይቻቸዋለሁ”
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

መርዋነል አስገርም እንዳስተላለፉት
“ኢብኒ ዑመር አንበርክከው ወደ ቂብላ ዞረው ሲፀዳዱ “የአብድራህማን አባት ሆይ! ይህን ተግባር ነብዩ ከልክለው አይደል?” አልኳቸው:: እሳቸውም “አዎን የተከለከለው ግን አውላላ ሜዳ ላይ ነው በአንተና በቂብላ መካከል ግርዶሽ ካለ ችግር የለውም፡፡”
(አቡ ዳውድ ዳረ ቁጥኒይና ሃኪም ዘግበውታል) አሉ::
ሆኖም ግን ክፍል ውስጥም ቢሆን ይህን አለማድረግ የተሻለ ነው፡፡

ሶስተኛ

መፀዳጃ ቤት የሚገባ ሰው ሊያሟላቸው የሚገባው ስርዓቶች

መፀዳጃ ለሚገባ ሰው የሚከተለውን ማለት የተወደደ ነው፦


"
بسم الله اللهم إني أعوذ بك من الخبث والخبائث"
“ቢስሚላሂ አሏሁመ ኢኒ አዑዙቢከ ሚነል ኹቡሲ ወል ኸባኢስ”
ትርጉሙ፦ ጌታዬ ከወንድም ሆነ ከሴት ሸይጣን ባንተ እጠበቃለሁ ማለት ነው::
አጠናቆ ሲወጣ ደግሞ፦
"
غفرانك"
“ጉፍሪነክ”2 ማለት::
ትርጉሙ፦ ጌታዬ ሆይ ማረኝ ማለት ነው::

ሲገባ ግራ እግርን ሲወጣ ደግሞ ቀኝን ማስቀደም፡፡
ወደ መሬት ዝቅ እስኪል ገላውን አለመግለፅ፡፡
አውላላ ሜዳ ላይ የሚፀዳዳ ከሆነ ከሰው ርቆና ከአይን ተሰውሮ መፀዳዳት፡፡
ለነዚህ ሁሉ ማሰረጃ ጃቢር እንዲህ በማለት የዘገቡት ሀዲስ ነው
“ከአላህ መልዕክተኛ ጋር ጉዞ ወጥተን ነበርና መፀዳዳት ሲፈልጉ ርቀው ከአይን ተሰውረው እንጂ አይፀዳዱም ነበር፡፡”
(አቡዳውድ እና ኢብኑማጃ ዘግበውታል)

ዓሊይ ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ እንዲህ ብለዋል
“በጋኔን እይታና በሰው ልጅ ሀፍረተ ገላ ግርዶሽ የሚሆነው መፀዳጃ ቤት ሲገባ “ቢስሚላህ ማለት” ነው፡፡”
(ኢብኑማጃ እና ቲርሚዚይ)
አነስ ባስተላለፉትም ሀዲስ
“የአላህ መልዕክተኛ መፀዳጃ ቤት ሲገቡ “ቢስሚላሂ አሏሁመ ኢኒ አዑዙቢከ ሚነል ኹቡሲ ወል ኸባኢስ” ይሉ ነበር፡፡”
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ዓኢሻ ባስተላለፉትም ሀዲስ
“ ነብዩ ከመፀዳጃ ቤት ሲወጡ “ጉፍሪነክ” ይሉ ነበር፡፡”
(አቡዳውድና ቲርሚዚይ)
ኢብኑ ዑመር ባስተላለፉት ሀዲስ
“ ነብዩ መፀዳዳት ሲፈልጉ ወደ መሬት ሳይቀርቡ ልብሳቸውን ከፍ አይሰበስቡም ነበር፡፡”
(አቡዳውድና ቲርሚዚይ)

አራተኛ

መፀዳዳት በፈለገ ግለሰብ ክልክል የሆኑ ነገሮች
በኩሬ ውሃ ላይ መፀዳዳት፦


ማስረጃው ጃቢር ባስተላለፈው ሀዲስ
“ነብዩ ኩሬ ውሃ ላይ መፀዳዳትን ከልክለዋል፡፡” (ሙስሊም ዘግበውታል)

ሲፀዳዱ ብልትን በቀኝ እጅ መንካትና በቀኝ እጅ ኢስቲንጃእ ማድረግ፦

ነብዩ እንዲህ ብለዋል
“ስትፀዳዱ ብልታችሁን በቀኝ እጅ እንዳትነኩ፤ በቀኝ እጃችሁም ኢስቲንጃእ እንዳታደርጉ::”
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)


መንገድ ላይ፣ ጥላ ስር፣ የአትክልት ቦታዎች ላይ፣ ፍሬያማ ዛፎች ስርና የውሃ መውረጃ ላይ መፀዳዳት አይፈቀድም፡፡

ለዚህ ማስረጃ ሙዓዝ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል
“ሶስት ለእርግማን የሚያዳርጉ ነገሮችን ተጠንቀቁ፡- በውሃ መውረጃ ፣ በአውራ ጐዳና እና በጥላ ስር መፀዳዳት፡፡”
(አቡዳውድና ኢብኑማጃ ዘግበውታል)


አቡሑረይራም ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል
“ ሁለት አስረጋሚዎችን ተጠንቀቁ” እነማን ናቸው ሲሏቸው “በሰዎች መንገድ ላይና በጥላቸው ስር መፅዳዳት”
(ሙስሊም ዘግበውታል)

በእንስሳ እዳሪ፣ በአጥንትና በምግብ ላይ መፀዳዳት፦

ጃቢር ባስተላለፉት ሀዲስ
“ነብዩ በአጥንት ወይም በእንስሳ እዳሪ መፀዳዳትን ከልክለዋል፡፡”
(ሙስሊም ዘግበውታል)

በሙስሊሞች የቀብር ቦታ መፀዳዳት፦
ነብዩ እንዲህ ብለዋል “በቀብሮች መካከልና በሱቆች መሃል መፀዳዳት ለውጥ የለውም (በገቢያ ህዝብ መሀል መፀዳዳት ክልክል እንደሆነ ሁሉ በቀብሮች መካከልም መፀዳዳት ክልክል ነው)፡፡”
(ኢብኑማጃ ዘግበውታል)

                                          አምስተኛ

                                በሚፀዳዳ ሰው የተጠሉ ተግባሮች

1,የሚፀዳዳ ሰው ንፋስ ወደሚነፍስበት አቅጣጫ ወደራሱ እንዳይመለስበት ሲባል መዞር የተጠላ ነው፡፡
2,መናገር የተጠላ ነው፦
ነብዩ እየተፀዳዱ አንድ ሰው በአጠገባቸው ሲያልፍ ሰላም ቢላቸውም እስኪጭርሱ ምላሽ አልሰጡትም፡፡ (ሙስሊም ዘግበውታል)
3,በሽንቁርና በመሳሰሉት ላይ መፀዳዳት የተጠላ ነው::
ቀታዳህ አብደላህ ኢብኑ ሰርጂስን ጠቅሰው እንደዘገቡት
“ነብዩ በሽንቁር ውሰጥ መፀዳዳት ከልክለዋል፡፡” ቀታዳ ሽንቁር ላይ መፀዳዳት ችግሩ ምን እንደሆነ ተጠይቀው “የጋኔኖች ማደሪያ ነው ይባላል” ብለዋል፡፡ (አቡዳውድ እና ነሳኢይ)
እንዲሁም ደግሞ እዚያ ውስጥ እንስሳ ኖሮ ሊጐዳ ወይም ጋኔን ኖሮ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል

5,የአላህ ስም ያለበትን ነገር አስፈላጊ ካልሆነ በቀር ይዞ መግባት የተጠላ ነው፡፡ ምክንያቱም “ነብዩ መፀዳጃ ቤት ሲገቡ ቀለበታቸውን አውልቀው ያስቀምጡ ነበር፡፡”
(አቡዳውድ፣ ነሳኢይ፣ ቲርሚዚይና ኢብኑ ማጃህ)

አስፈላጊ ከሆነ ወይም ለአስቸጋሪ ጉዳይ ሲባል ለምሳሌ መጥፋቱ መሰረቁ ወይም መረሳቱ የሚሰጋ ከሆነ ይዞ መግባት ችግር አይኖረውም፡፡
ቅዱስ ቁርአንን ግን በግልፅም ይሁን በውስጥ ደብቆ ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡ ምክንያቱም የተከበረ የአላህ ቃል በመሆኑ መፀዳጃ ቤት ይዞ መግባት እንደማሳነስ ስለሚቆጠር ነው፡፡




SHARE THIS POST   

  • Facebook
  • Twitter
  • Myspace
  • Google Buzz
  • Reddit
  • Stumnleupon
  • Delicious
  • Digg
  • Technorati
Author: Mohammad
Mohammad is the founder of STC Network which offers Web Services and Online Business Solutions to clients around the globe. Read More →

0 comments: