Download this Blogger Template by Clicking Here!

Ad 468 X 60

Saturday 23 August 2014

Widgets

ዉዱእ

ትምህርት ቁጥር 1
ዉዱእ
ትርጉሙና ሸሪዓዊ ድንጋጌው

ውዱእ የተሰኘው የዓረብኛ ቃል ቋንቋዊ ትርጉሙ ማማርና መፅዳት ማለት ነው፡፡

ሸሪዓዊ ትርጉሙ፡-
ውሃን አራት አካሎች(አራት አካሎች ፊት፣ እጆች፣ ራስና እግሮች) ላይ ሸሪዓው በወሰነው መልኩና አላሀን ለማምለክ ታስቦ መጠቀም ነው፡፡

ሸሪዓዊ ድንጋጌው፡-
ሰላትንና መሰል ውድእ የሚያስፈልጋቸውን እንደጠዋፍ፣ ቁርአንን መንካትና የመሳሰሉትን ለመፈፀም በፈለገና ውዱእ በሌለው ሰው ላይ ግዴታ ነው፡፡

ትምህርት ቁጥር 2
ዉዱእ ዋጂብ (ግዴታ) የሚሆነው መች ነው?

ግዴታ ለመሆኑ ማስረጃው የሚከተለው የአላህ ቃል ነው፡-
‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወደ ሶላት በቆማችሁ (ለመቆም ባሰባችሁ) ጊዜ ፊቶቻችሁን፣ እጆቻችሁንም እስከ ክርኖች እጠቡ፡፡ ራሶቻችሁንም (በውሃ) አብሱ፡፡ እግሮቻችሁንም እስከ ቁርጭምጭሚቶች (እጠቡ)፡፡ (ሴት ጋር በመገናኘት ወይም በሌላ ምክንያት «ጀናባ») ብትኾኑ (ገላችሁን) ታጠቡ፡፡ በሽተኞች ወይም በጉዞ ላይ ብትኾኑም ወይም ከእናንተ አንዳችሁ ከዓይነ ምድር ቢመጣ ወይም ሴቶችን ብትነካኩና ውሃን ባታገኙ ንጹሕን የምድር ገጽ አስቡ ፡፡ ከሱም ፊቶቻችሁንና እጆቻችሁን አብሱ፡፡ አላህ በእናንተ ላይ ምንም ችግር ሊያደርግ አይሻም፡፡ ግን ታመሰግኑ ዘንድ ሊያጠራችሁና ጸጋውን በእናንተ ላይ ሊሞላ ይሻል፡፡›› (አል ማኢዳህ 6)
ነብዩ እንዲህ ብለዋል
“አላህ ያለ ውዱእ ሰላትን አይቀበልም፣ ከተሰረቀ ዕቃም ምፅዋትን አይቀበልም” (ሙስሊም ዘግበውታል)
በሌላም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል
“አላህ ውዱእ የሌለውን ውዱእ እስካላደረገ ሰላቱን አይቀበለውም” (ሙስሊም ዘግበውታል)
ከሙስሊሞች ውስጥ ይህንን የተቃወመ አንድም ሰው አይታወቅም፡፡ ስለዚህ የውዱእ ግዴታነት በቁርአን በሀዲስና በኡለማዎች ስምምነት (ኢጅማዕ) የፀደቀ ነው፡፡
ግዴታ የሚሆነው መች ነው? ለሚለው ደግሞ፡- የሰላት ወቅት ሲደረስ ወይም ደግሞ ውዱእ መስፈርት

የሆነበትን ነገር ለምሳሌ
ጠዋፍ ለማድረግና ቁርአንን ለመንካት የመሳሰሉትን ስራ መስራት ሲፈልግ ነው፡፡
ግዴታ የሚሆንበት ሰው ደግሞ
ሙስሊም የሆነ፣
አካለ መጠን የደረሰና
አእምሮው ጤነኛ የሆነ ሰው ላይ ነው፡፡
ትምህርት ቁጥር 3
ውዱእ መስፈርቶቹ

ውዱእ ትክክለኛ እንዲሆን የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡-
1. ሙስሊም፡ አእምሮ ጤናማ የሆነና ጥሩና መጥፎ የሚለይ ካፊርና እብድ ሰላታቸው ትክክለኛ ያልሆነ ሲሆን ህፃን ከመለያ እድሜው በፊት ቢሰግድም ሰላቱ አይቆጠርም፡፡
2. ኒያ (በልብ ማሰብ)፡ ለዚህ ማሰረጃ የሚከተለው ሀዲስ ነው
“ስራዎች ትክክል የሚሆኑት በኒያ ነው” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ኒያን በምላስ መናገር ግን ከነብዩ መመሪያ የሌለ ነው፡፡
3. ንፁህና የሚያፀዳ ውሃን መጠቀም፦ ይህ ባለፉ ት/ቶች ላይ በውሃ ርዕስ ስር ተጠቅሷል፡፡ በነጃሳ ውሃ ውዱእ ማድረግ አይቻልም፡፡
4. ውሃ ወደ አካል እንዳይደርስ የሚያግዱ ነገሮችን ማስወገድ፡፡ ለምሳሌ ሻማ፣ ሊጥ፣ የጥፍር ቀለምና የመሳሰሉት::
5. አስፈላጊ ከሆነ ኢስቲንጃእ ወይም ኢስቲጅማር ማድረግ::
6. ማከታተል::
7. ቅደም ተከተሉን መጠበቅ
8. ማጠብ ግዴታ የሚሆኑ አካሎችን ሁሉ ማጠብ፡፡
ትምህርት ቁጥር 4

በውዱዕ ጊዜ የግድ መታጠብ ያለባቸው አካሎች ስድስት ናቸው፦

1. ፊትን ሙሉ በሙሉ ማጠብ፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹ወደ ሶላት በቆማችሁ (ለመቆም ባሰባችሁ) ጊዜ ፊቶቻችሁን…(እጠቡ)፡፡››(አል ማኢዳህ 6)
መጉመጥመጥና በአፍንጫ መሳብ ከፊት ማጠብ ጋር የሚካተቱ ናቸው፡፡

2. እጆችን ከነክርኖች ማጠብ፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹እጆቻችሁንም እስከ ክርኖች እጠቡ፡፡››(አል ማኢዳህ 6)

3. ሙሉ ራስን ከጆሮ ጋር አብሮ ማበስ፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹ራሶቻችሁንም (በውሃ) አብሱ፡፡››(አል ማኢዳህ 6)
ነብዩም “ጆሮ ከራስ የሚካተት ነው” ብለዋል ከፊል ራስን አብሶ ከፊሉን መተው በቂ አይደለም፡፡

4. እግሮችን እስከ ቁርጭምጭሚቶች ድረስ ማጠብ፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹እግሮቻችሁንም እስከ ቁርጭምጭሚቶች (እጠቡ)››(አል ማኢዳህ 6)

5. ቅደም ተከተሉን መጠበቅ፦ ምክንያቱም አላህ በቅደም ተከተል ስለገለፃቸውና ነብዩም አላህ በገለፀው መልኩ በቋሚነት ስለተገበሩ፡፡
ቅደም ተከተሉ አብደላህ ኢብኑ ዘይድ ከነብዩ ባስተላለፉት ሀዲስ መሰረት “ፊት ከዚያ እጆች ቀጥሎ ራስ እና በመጨረሻም እግሮች ናቸው፡፡

6. ማከታተል፦ ማለትም አንዱን አካል አጥቦ ሳይዘገይ ወደ ሌላው አካል ማለፍ፡፡ ለዚህ ማሰረጃው ነብዩ ውዱእ ሲያደርጉ በማከታተል ነበር፡፡ ኻሊድ ኢብኑ ሚዕዳን ባስተላለፉትም ሀዲስ
“ነብዩ አንድ ሰው እየሰገደ ሳለ እግሩ ላይ ውሃ ያልደረሰው ዲርሐም የሚያህል ቦታ ደርቆ አዩትና ውዱኡን በድጋሚ እንዲያደርግ አዘዙት፡፡” (አህመድና አቡዳውድ ዘግበውታል)
ይህ ሀዲስ ውዱእን በማከታተል ማድረግ ግዴታ እንደሆነ ይጠቁማል፡፡ ምክንያቱም ግዴታ ባይሆን ኖሮ ውሃ ያልደረሰውን እንዲያጥብ እንጂ በድጋሚ እንዲያደርግ አያዙትም ነበር፡፡

ትምህርት ቁጥር 5
የውዱእ ሱናዎች

ሱና ማለት ቢሰራ አጅር የሚያስገኝ ቢተውም ችግር የሌለው ሲሆን የውዱእ ሱናዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. ሲጀመር “ቢስሚላሂ” ማለት
ነብዩ እንዲህ ብለዋል “ቢስሚላሂ ያላለ ውዱእ የለውም”
2. ጥርስን መፋቅ፡
ነብዩ እንዲህ ስላሉ “ህዝቦቼን ማስቸገር ባይሆንብኝ ኖሮ ከእያንዳንዱ ውዱእ ጋር ጥርሳቸውን እንዲፍቁ አዛቸው ነበር፡፡” (ቡኻሪ ዘግበውታል)
3. የውዱእ መጀመሪያ ላይ መዳፎችን ሶስት ጊዜ ማጠብ፡፡ ስነብዩ የውዱእ አደራረግ ሁኔታ እንደተነገረው መዳፎቻቸውን ያጥቡ ነበር፡፡
4. ፆመኛ ካልሆነ በስተቀር በደንብ መጉመጥመጥና በደምብ በአፍንጫ ውሃን መሳብ ስለ ነብዩ ውዱእ ሁኔታ በተዘገበበት ሀዲስ “ነብዩ ተጉመጠመጡ በአፍንጫቸውም ውሃን ሳቡ”
በሌላም ሀዲስ ነብዩ እንዲህ ብለዋል
“ፆመኛ ካልሆንክ በስተቀር በአፍንጫ በደምብ ሳብ” (አቡዳውድ እና ነሳኢይ ዘግበውታል)
5. አካሎችን እያሹ ማጠብና እጅብ ያለን ፂም በጣት በመፈልፈል ውሃን ወደ ውስጥ ማድረስ፡፡ “ነብዩውዱእ ሲያደርጉ ክርኖቻቸውን ያሹ ነበር”(ኢብኑ ሂባን፣ በይሐቂይ፣ ሃኪም፣ኢብኑ ኹዘይማና አህመድ ዘግበውታል)
እንዲሁም
“ውሃ ከአገጫቸው ስር በመክተት ፂማቸውን ይጐነጉኑበት ነበር” (አቡዳውድ ዘግበውታል)
6. እግሮችና እጆች ሲታጠቡ በቀኝ መጀመር፦ ምክንያቱም ነብዩ “ጫማ ሲያደርጉ፣ ፀጉራቸውን ሲያበጥሩ፣ ውዱእ ሲያደርጉና ማንኛውንም ጉዳያቸውን ሲፈፅሙ በቀኝ መጀመር ይወዱ ነበር” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

7. ፊት እጅና እግሮች ሲታጠቡ ሶስት ሶስት ጊዜ ማድረግ፦ ግዴታው አንዳንድ ጊዜ ማድረግ ሲሆን ሶስት ሶስት ጊዜ ማድረግ ግን የተወደደ ነው፡፡ ነብዩ ውዱእ አንዳንዴም ሁለት ሁለቴ ሶስት ሶስቴ ጊዜም ያደርጉ ነበር”
8. ከውዱእ በኋላ ከነብዩ የተላለፈውን ዚክር ማለት፦ እንዲህ ብለዋል
“ማንኛውም ሰው ውዱእን አሟልቶ ይህን ዚክር ካለ ስምንቱ የጀነት በሮች ይከፈቱለትና በፈለገው ይገባል፦
"
أشهد أن لا إله إلا الله وحده لا شريك له وأشهد أن محمدا عبده ورسوله"
“አሽሐዱ አንላኢላሃ ኢለላህ ወህደሁ ላሸሪከለሁ ወአሽሐዱ አነ ሙሀመደን አብዱሁ ወረሱሉህ”
(ከአላህ ሌላ መመለክ የሚገባው እንደሌለና መሐመድም ባሪያውና መልዕክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለሁ፡፡)

ትምህርት ቁጥር 6
የውዱእ አፍራሾች ስድስት ናቸው፦

1. ከሽንትና ሰገራ መውጫ ቦታዎች የሚወጣ ማንኛውም ነገር፡፡ ከሁለቱ አቅጣጫ ሊወጡ የሚችሉት ነገሮች ሽንት፣ ሰገራ፣ የፍትወት ጠብታ፣ የስሜት ፈሳሽና የበሽታ ደም ይሆናሉ፡፡ ለዚህ ማስረጃ አላህ እንዲህ ይላል፡-
‹‹…ወይንም ከእናንተ አንዱ ከዓይነምድር ቢመጣ…›› (ኒሳእ 43)
ነብዩ ከአካሉ ትንፋሽ መውጣት አለመውጣቱን ለተጠራጠረው ሰው እንዲህ ብለውታል
“ድምፅ ካልሰማ ወይም ካልሸተተው ሰላቱን እንዳያቋርጥ፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም)

2. ከተቀረው ሰውነት ነጃሳ መውጣት፦ የሚወጣው ሽንት ወይም ሰገራ ከሆነ ከላይ እንደሳለፍነው ውዱእ ያፈርሳል፡፡ ከሁለቱ ሌላ ለምሳሌ ደም ወይም ትውከት ከሆነ ግን በብዛት ከወጣ ለጥንቃቄ ውዱእ ማድረግ የተሻለ ሲሆን አነስተኛ ከሆነ ግን ውዱእ አያስፈልገውም፡፡

3. አእምሮን መሳት ወይም በእንቅልፍ በአዙሪት አእምሮ መሸፈን፦ ነብዩ እንዲህ ብለዋል
“በሰገራ በሽንት ወይም በእንቅልፍ ውዱእ የጠፋ ከሆነ ግን ….” በሌላም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል “አይን የመቀመጫ ማሰሪያ ነውና የተኛ ውዱእ ማድረግ አለበት፡፡” (አቡ ዳውድና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል)
እብደት፣ አዙሪትና ስካር ውዱእን እንደሚያፈርሱ ዑለማዎች ሁሉም ተስማምተዋል፡፡
ውዱእ የሚያጠፋው እንቅልፍ ጭልጥ ያለ ምንም እራሱን የማያውቅበት ከሆነ ነው፡፡ ቀለል ያለ እንቅልፍ ግን ውዱእ አያፈርስም፡፡ ለዚህ ማሰረጃ “ሰሃባዎች
ሰላትን ሲጠባበቁ እንቅልፍ ያንገላጃቸውና ሲደርስ ተነስተው ውዱእ ሳያደርጉ ያሰግዱ ነበር” (ሙስሊም ዘግበውታል)

4. ብልትን ያለምንም ግርዶሽ መንካት፡ ለዚህ ማስረጃ ቡስራ ቢንት ሰፍዋን ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ እንዲህ ብለዋል
“ ብልቱን የነካ ውዱእ ያድርግ” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
አቡ አዩብና ኡሙ ሀቢባም በዘገቡት ሀዲስ “ብልቱን የነካ ውዱእ ያድርግ” ብለዋል (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

5. የግመል ስጋ መብላት፡ ጃቢር ባስተላለፉት ሀዲስ “አንድ ሰው የአላሀ መልዕክተኛን እንዲህ በማለት ጠየቃቸው “የበግ ስጋ ከበላን በኋላ ውዱእ ማድረግ አለብን?” እሳቸውም “ ከፈለግክ ውዱእ አድርግ ከፈለግክ አታድርግ” አሉት ቀጥሎም “የግመል ስጋ በልተንስ ውዱእ እናድርግ?” ሲላቸው “አዎን ከግመል ስጋ በኋላ ውዱእ አድርግ አሉ፡፡”

6. እስልምናን ትቶ ወደ ሌላ ሀይማኖት መመለስ፦ አላህ እንዲህ ይላል፡-
‹‹ከእምነትም የሚመለስ ሰው በእርግጥ ሥራው ተበላሸ፡፡›› (አል ማኢዳህ 5)
ገላን መታጠብ የሚያስገድዱ ነገሮች ሁሉ ሞት ሲቀር ውዱእንም ያስገድዳሉ፡፡

ትምህርት ቁጥር 7

====[ውዱእ ማድረግ ግዴታ የሚሆንላቸው ነገሮች]=======

አንድ ሰው የሚከተሉትን ነገሮች ለመስራት ሲፈልግ በቅድሚያ ውዱእ ማድረግ አለበት፦
1. ሰላት ለመስገድ፦ ኢብኑ ዑመር በዘገቡት ሀዲስ ነብዩ እንዲህ ብለዋል
“አላህ ያለውዱእ ሰላትን አይቀበልም ከተሰረቀም ነገር ምፅዋትን አይቀበልም፡፡” ( ሙስሊም ዘግበውታል)

2. ግዴታም ይሁን ሱና ካዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ለማድረግ፦
ነብዩ “በቅድሚያ ውዱእ አድርገው ከዚያ በካዕባ ዙሪያ ጠዋፍ አድረገዋል፡፡” ( ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

እንዲሁም ነብዩ እንዲህ ብለዋል “በካዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ማድረግ ሰላት ነው፡፡ ልዩነቱ ግን ጠዋፍ ላይ መናገር አላህ ፈቅዷል፡፡” እንዲሁም ደግሞ “የወር አበባ ያለባትን ሴት እስክትፀዳ ድረስ ጠዋፍ እንዳታደርግ ከልክለዋል”
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

3. ቁርአንን ያለግርዶሽ ለመንካት፦ አላህ እንዲህ ብሏል
‹‹የተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም፡፡›› (ዋቂዓህ 79)
ነብዩም እንዲህ ብለዋል “ቁርአንን ንፁህ እንጂ እንዳይነካ”

ትምህርት ቁጥር 8

===*በቅድሚያ ውዱእ ማድረግ የሚወደድላቸው ተግባሮች*===

1. አላህን ለማውሳትና ቁርአንን ለማንበብ

2. ለእያንዳንዱ ሰላት፦ ነብዩ ዘውትር ውዱእ ያደርጉ ነበር፡፡ አነስ በአስተላለፉት ሀዲስ “ነብዩ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) ለእያንዳንዱ ሰላት ውዱእ ያደርጉ ነበር፡፡” (ቡኻሪ ዘግበውታል)

3 ግንኙነት የፈፀመ ሰው መድገም ወይም መተኛት ወይም ደግሞ መብላት መጠጣት ከፈለገ ውዱእ ቢያደርግ ይወደዳል፡፡ አቡ ሰኢድ አልኹድሪይ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል
“አንድ ሰው ሚስቱን ተገናኝቶ በድጋሚ መመለስ ከፈለገ ውዱእ ያድርግ፡፡” (ሙስሊም ዘግበውታል)
ዓኢሻ ባስተላለፉትም ሀዲስ
“ነብዩ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም)
ግብረስጋ ግንኙነት ከፈፀሙ በኋላ መተኛት ሲፈልጉ በቅድሚያ ውዱእ ያደርጉ ነበር፡፡” (ሙስሊም ዘግበውታል)
በሌላ ዘገባ ደግሞ
“መብላት ወይም መተኛት ሲፈልጉ” በሚል (ከሙስሊም) ተዘግቧል

4. ከገላ ትጥበት በፊት ውዱእ ማድረግ፦ ዓኢሻ ባስተላለፉት ሀዲስ “ነብዩ ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ ገላቸውን ሲታጠቡ በቅድሚያ ውዱእ ያደርጉ ነበር፡፡

5. ለመተኛት፦ በራእ ኢብን ዓዚብ እንዳስተላለፉት ነብዩ እንዲህ ብለዋል
“መኝታ ቦታህ ስትመጣ ለሰላት የምታደርገውን ውዱእ አድርግ ከዚያ በቀኝ ጐንህ ተኛ ….” ( ቡኻሪ ዘግበውታል)

SHARE THIS POST   

  • Facebook
  • Twitter
  • Myspace
  • Google Buzz
  • Reddit
  • Stumnleupon
  • Delicious
  • Digg
  • Technorati
Author: Mohammad
Mohammad is the founder of STC Network which offers Web Services and Online Business Solutions to clients around the globe. Read More →

0 comments: