Download this Blogger Template by Clicking Here!

Ad 468 X 60

Monday 25 August 2014

Widgets

የወር አበባ

                             ትምህርት ቁጥር 1

                                      #የወር_አበባ

አንደኛ
የወር አበባ ጅማሬና መጨረሻ ጊዜ
ሴት ልጅ ዘጠኝ አመት እድሜ ሳይሞላት የወር አበባ ደም ሊኖርባት አይችልም፡፡ ምክንያቱም የትኛዋም ሴት ከዚህ እድሜ በፊት የወር አበባ ገጥሟት አያውቅም፡፡ ከዓኢሻም የሚከተለው ንግግራቸው ተዘግቧል
“ልጃገረድ ዘጠኝ አመት ከሞላት ደረሰች ማለት ነው፡፡”(ቲርሚዚይና በይሐቂይ)
በአብዛኛው ደግሞ ከሀምሳ አመት በኋላ የወር አበባ ደም አይኖርም፡፡ ከዓኢሻ እንደተዘገበው “አንድ ሴት ሀምሳ አመት ከሞላት የወር አበባ ጊዜዋን አልፋለች፡፡” (አልሙግኒ 1\4ዐ6)

ሁለተኛ
አነስተኛውና አብዛኛው የወር አበባ ጊዜ
ከዑለማዎች አቋም ትክክለኛው ለወር አበባ ብዙ ትንሽ ቀነ ገደብ አለመወሰን ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ በሴቶች ተለምዶ የሚወሰን ነው፡፡

ሶስተኛ
የተለመደው የወር አበባ ጊዜ
በተለምዶ በአብዛኛው ጊዜ የወር አበባ የሚቆየው ስድስት ወይም ሰባት ቀናት ነው፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል
“የወር አበባሽን እስከ ስድስት ወይም ሰባት ቀን ጠብቂውና ታጥበሽ ሀያ ሶስት ወይም ሀያ አራት ቀናት ስገጂ፡፡”(አቡዳውድና ቲርሚዚይ)
                                   ትምህርት ቁጥር 2

                     በወር አበባና በወሊድ ደም ወቅቶች የሚከለከሉ ነገሮች

1. በብልት ግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም፦
አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹ሴቶችንም በወር አበባ ጊዜ ራቋቸው፡፡ ንጹሕ እስከሚኾኑም ድረስ አትቅረቡዋቸው፡፡›› (አል በቀራህ 222)
ነብዩም (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ይህ አንቀፅ የወረደ ጊዜ ሲያብራራሩት እንዲህ ብለዋል
“ከግብረ ስጋ ግንኙነት ውጪ ሁሉን ነገር መፈፀም ትችላላችሁ፡፡” ብለዋል:: (ሙስሊም ዘግበውታል)

2. የፍቺ ስነስርዓት፡- አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹ሴቶችን መፍታት ባሰባችሁ ጊዜ፤ ለዒዳቸው ፍቱዋቸው፡፡›› (አል ጠላቅ 1)
የዑመር ልጅ ዓብደላህ ሚስታቸው የወር አበባ ላይ እያለች ፈተዋት ስለነበር ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ለዑመር እንዲህ “ሚስቱን እንዲመልሳት እዘዘው….” አሉት:: (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

3. ሰላት መስገድ፡-
ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ለፋጢማ ቢንት ጀህሽ
“የወር አበባሽ ሲመጣ ሰላት አቁሚ” ብለዋታል:: (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

4. መፆም፡-
ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል
“ሴት ልጅ የወር አበባዋ በሚመጣ ጊዜ አትሰግድም አትፆምም”( ቡኻሪ ዘግበውታል)
5. ካዕባን ጠዋፍ ማድረግ፡- ዓኢሻ የወር አበባዋ ሲመጣ ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋታል
“እስክትፀጂ ድረስ ካዕባን ጠዋፍ ከማድግ ውጭ የተቀሩትን የሀጅ ስራዎች ሁሉ ፈፅሚ፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
6. ቁርአን ማንበብ፡- ይህ የአብዛኞች ሰሃባዎች፣ ታቢዕዮችና ከነሱም ቡኋላ የመጡ ዑለማዎች አቋም ነው፡፡ ሆኖም ግን ለምሳሌ ቁርአንን በቃሏ የሸመደደች ሆኗ ለማስታወስ ወይም አስተማሪ ሆና ለተማሪዎች ለማስቀራት ለመሳሰሉ ጉዳዮች ቁርአን መቅራት አስፈላጊ ሆኖ ካገኘችው ማንበብ ትችላለች፡፡ ይህ ካልሆነ ግን አንዳንድ ዑለማዎች እንዳሉት ባታነብ ይመረጣል፡፡
7. ቁርአን መንካት፡-
አላህ እንዲህ ብሏል
‹‹የተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም፡፡›› (አል ዋቂዓ 79)
8. መስጂድ ውስጥ መቀመጥ፡- ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል
“መስጂድን ጀናባና የወር አበባ ላለባቸው አልፈቅድም “(አቡዳውድ ዘግበውታል)
እንዲሁም
“ዓኢሻ የወር አበባ ላይ ሆና ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ከመስጂድ ወደ ክፍልዋ ራሳቸውን አስገብተውላት ታበጥርላቸው ነበር፡፡”(ቡኻሪ ዘግበውታል)
መስጂድ ውስጥ በመንጠባጠብ የሚበክል ከሆነ ማለፍም አይፈቀድላትም፡፡ ይህ ካልሆነ ገን አትከለከልም፡፡

                             ትምህርት ቁጥር 3
               
                      #የወር_አበባ_የሚያስገድዳቸው_ነገሮች

አምስተኛ
የወር አበባ የሚያስገድዳቸው ነገሮች
1. ገላ ትጥበት፡- ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል
“የወር አበባ የሚቆይብሽን ጊዜ ያህል ሰላት አቁሚና ከዚያ ታጥበሽ ስገጂ፡፡”(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
2. አቅመ ሄዋን መድረስ፦ ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል
“ የወር አበባ የምታይ ሴት ያለ ሻሽ ሰላት ብትሰግድ አላህ አይቀበላትም፡፡” (አቡዳውድ ቲርሚዚይና ኢብኑ ማጃህ)
በዚህ ሀዲስ ላይ የወር አበባ የምታይን ሴት ሂጃብን አስገድደዋታል፡፡ ግዴታ ደግሞ የሚጀምረው ለአቅመ ሄዋን በመድረስ ነው፡፡ ስለዚህ የወር አበባ መምጣት የመድረስ ምልክት ነው ማለት ነው፡፡
3. ቀን ቀጠሮን በወር አበባ መቁጠር፡- የወር አበባ የምታይ ሴት ባሏ ከፈታት ሁለተኛ ሌላ ከማግባቷ በፊት የምትቆየውን ጊዜ መቁጠር ያለባት በወር አበባዋ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹የተፈቱ ሴቶችም ነፍሶቻቸውን (ከማግባት) ሦስትን ቁርእ ይጠብቁ፡፡›› (አል በቀራህ 228)
4. የማህፀን መጥራት የሚወሰነው በወር አበባ በመቁጠር ነው፡፡
ማሳሰቢያ፦ ሴት ልጅ ከወር አበባዋ ወይም ከወሊድ ደም ፀሐይ ከመጥለቁ በፊት ከፀዳች የዕለቱን ዙህርና አስር ሰላት ቀዷ መስገድ ሲኖርባት ጐህ ከመቅደዱ በፊት ከፀዳች ደግሞ የሌሉቱን መግሪብና ዒሻ ሰላቶች ቀዷ መስገድ አለባት፡፡ ምክንያቱም ችግሮች በሚገጥሙ ጊዜ የሁለተኛው የሰላት ወቅት ለአንደኛው ይሆናል፡፡ ይህ የማሊክ ሻፊኢይ አህመድና የአብዛኞች ዑለሞች አቋም ነው፡፡
                                ትምህርት ቁጥር 4

                            #አብዛኛውና አነስተኛው የወሊድ ደም ጊዜ

ስድስተኛ
አብዛኛውና አነስተኛው የወሊድ ደም ጊዜ
ለአነስተኛ የወሊድ ደም ጊዜ ገደብ ስለሌለው ያለው ሁኔታ ይወስነዋል፡፡ አንዳንዴ በዝቶ ሌላ ጊዜ ደግሞ አንሶ ይገኛል፡፡ ብዙን ግን አርባ ቀን ነው፡፡ ቲርሚዚይ እንዲህ ብለዋል “የወሊድ ደም ያለባት ሴት ለአርባ ቀን ሰላት እንደምታቆም ዑለማዎች ተስማምተዋል፡፡ ነገር ግን ከዚያ በፊት ከፀዳች ታጥባ መስገድ ይኖርባታል፡፡” ኡሙ ሰለማ ባስተላለፉትም ሀዲስ
“በነብዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ዘመን የወሊድ ደም ያለባት አርባ ቀን ድረስ ሰላት ከመስገድ ትታቀብ ነበር፡፡”(አቡዳውድ ቲርሚዚይና ኢብኑ ማጃህ)
ሰባተኛ
የበሽታ ደም
የወር አበባን ጊዜ ማይጠብቅ ከደም ስር መበጠጥ የሚፈስ ደም ሲሆን ከወር አበባ ጋር በአይነትም ሆነ በሸሪዓዊ ብይናቸው ይለያያሉ፡፡
ይህ ደም በመፍሰሱ ጠሃራ ከመሆኗ የማትወገድ በመሆኗ ሰላት ፆምም ሆነ ግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም አትከለከልም፡፡ ለዚህ ማስረጃው ፋጢማ ቢንት አቢጀህሽ ያስተላለፉት ሀዲስ ነው፡፡

“የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሆይ! እኔ የወር አበባ ደም ሳያቋርጥ ይፈሰኛልና ሰላት መተው አለብኝ? በማለት ስትጠይቃቸው እንዲህ በማለት መለሱላት
“አይ ይህማ የወር አበባ ሳይሆን የተበጠሰ የደም ስር ነው የተለመደው የወር አበባሽ ሲመጣ ሰላት አቁሚና ሲሄድ ደምሽን አጥበሽ ስገጅ፡፡”(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

የተለመደው የወር አበባ ጊዜዋ ሲያበቃ ገላዋን መታጠብ ግዴታዋ ሲሆን ለበሽታ ደሙ ደግሞ ሀፍረተ ገላዋን አጥባ የደም መውጫውን እንደ ጥጥ መሰል ነገር በመጠቀም አሽጋ ደም እንዳይፈስ ማድረግ አለባት፡፡ ወቅታዊ የሆነውን “ሞዴስ” ብትጠቀምም የተሻለ ነው፡፡ ከዚያ ለእያንዳንድ የሰላት ወቅት ውዱእ እያደረገች ትሰግዳለች፡፡
                               ትምህርት ቁጥር 5

                         #የወር_አበባ_የሚያስገድዳቸው_ነገሮች

የበሽታ ደም የምታይ ሴት ሶስት አይነት ሁኔታዎች ይኖራታል፡-

አንደኛ፦ የወር አበባ መምጫ ጊዜዋ እርሷ ዘንድ የታወቀ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ከሆነ በተለመደው ጊዜ የሚመጣውን ደም የወር አበባ አድርጋ ትቆጥረውና ሰላትና ፆምን ታቆማለች ይህ ጊዜዋ ሲያበቃ ደግሞ ታጥባ ትሰግዳለች፡፡ ከዚህ ውጪ ያለውን ደም እንደ በሽታ ደም ትቆጥራለች፡፡ ለዚህ ማሰረጃው ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ለኡሚ ሀቢባ እንዲህ በማለት የተናገሩት ሀዲስ ነው

“የወር አበባሽ የሚቆይብሽን ጊዜ ያህል ሳትሰግጂ ቆይና ከዚያ ታጥበሽ ስገጅ፡፡”(ሙስሊም ዘግበውታል)

ሁለተኛ፦ የተለመደ ጊዜ ከሌላትና ነገር ግን የወር አበባዋን ከበሽታ ደም የምትለይ ከሆነ ለምሳሌ የወር አበባዋ ጥቁር ወፍራም ሽታ ያለው ሆኖ የወር አበባን ባህሪ የያዘ ከሆነና የበሽታ ደሟ ደግሞ ቀይ ቀጭን ሽታ የሌለው ሆኖ የሌሎችን ደም ባህሪ የያዘ ከሆነ እንዲህ አይነቷ ሴት ሁለቱን በመለየት ትጓዛለች፡፡ ለዚህ ማስረጃው ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ለፋጢማ ቢንት አቢ ሁበይሽ እንዲህ ያሏት ነው
“ የወር አበባ ደም ከሆነ ጥቁር ሽታ ያለው ነው ይሄኔ ሰላት ከመስገድ ተቆጠቢ ከዚህ ውጭ ከሆነ ግን ውዱእ አድርገሽ ስገጅ ምክንያቱም ይህ ከደም ስር መበጠበስ የሚመነጭ ነው፡፡” (አቡዳውድና ሃኪም ዘግበውታል)

ሶስተኛ፦ የተለመደ ጊዜ ከሌላትና ደሞችንም መለያ ከሌላት የአብዛኞች ሴቶችን ተለምዶ በመውሰድ ስድስት ወይም ሰባት ቀናት ሰላትና ፆምን ታቆምና ከዚያ ታጥባ ሰላተና ፆሟን ትቀጥላለች፡፡ ለዚህም ማስረጃው ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ለሀምና ቢንት ጀህሽ እንዲህ ያሏት ነው
“ይህ የሸይጧን እንግጫ ነው የወር አበባሽን ስድስት ወይም ሰባት ቀናት አድረጊውና ከዚያ ስትፀጂ ሰላትና ፆምሽን ቀጥይ ይህ ለአንቺ በቂ ነው፡፡”(አቡዳውድና ቲርሚዚይ ዘግበውታል)

SHARE THIS POST   

  • Facebook
  • Twitter
  • Myspace
  • Google Buzz
  • Reddit
  • Stumnleupon
  • Delicious
  • Digg
  • Technorati
Author: Mohammad
Mohammad is the founder of STC Network which offers Web Services and Online Business Solutions to clients around the globe. Read More →

0 comments: