Download this Blogger Template by Clicking Here!

Ad 468 X 60

Monday 25 August 2014

Widgets

ገላ ትጥበት ሸሪዓዊ ድንጋጌውና ማስረጃው

                                    ትምህርት ቁጥር 1

                         #ገላ_ትጥበት_ሸሪዓዊ_ድንጋጌውና_ማስረጃው

1. ትርጉሙ፦
ሸሪዓው በሚፈልገው መልኩና አምልኮ ታስቦ ሙሉ አካልን በውሃ ማዳረስ ማለት ነው::

2 ሸሪዓዊ ድንጋጌው ፡-
ገላን ለመታጠብ የሚያስገድዱ ነገሮች ሲፈጠሩ መታጠብ ግዴታ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹(ሴት ጋር በመገናኘት ወይም በሌላ ምክንያት «ጀናባ») ብትኾኑ (ገላችሁን) ታጠቡ፡፡ ›› (አል ማኢዳህ 6)
ሰሃቦች ከነብዩ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) ያስተላለፏቸው የአሰተጣጠብ ሁኔታን የሚገልፁ ሀዲሶች የትጥበትን ግዴታነት የሚጠቁሙ ናቸው፡፡ የተወሰኑትን ወደፊት እንጠቅሳለን፡፡

3. ትጥበትን ግዳጅ የሚያደርጉ ነገሮች፦
1. የፍትወት ጠብታ መፍሰስ፡- ገላን መታጠብ ግዴታ የሚያደርገው የፍትወት ጠብታ በሀይልና በስሜት ሲወጣ ነው፡፡
አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹(ሴት ጋር በመገናኘት ወይም በሌላ ምክንያት «ጀናባ») ብትኾኑ (ገላችሁን) ታጠቡ፡፡ ›› (አል ማኢዳህ 6)
ነብዩም (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) ለዓሊይ እንዲህ ብለዋል
“ውሃን ካፈሰስክ ገላህን ታጠብ፡፡”(አቡዳውድ ዘግበውታል)
መኝታ ላይ የነበረ ሰው ግን ፈሳሹ ከስሜት ጋር መሆን አለበት አይባልም፡፡ ምክንያቱም መኝታ ላይ ያለ ይህ ስሜት ላይሰማው ይችላል፡፡ ነብዩ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) እንዲህ በመባል ሲጠየቁ
“ሴት ልጅ በህልሟ ግብረ ስጋ ግንኙነት ስትፈፅም ካየች ገላዋን መታጠብ አለባትን?”
“ፈሳሽ ካየች አዎን” ብለዋል፡፡
ከላይ የተጠቀሰው ሁሉ ዑለማዎች የተስማሙባቸው ናቸው::

2. የወንድ ብልት እስከ ክርክሩ ድረስ በሴቷ ብልት ከገባ፦
ነብዩ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) እንዲህ ብለዋል፡-
“በአራት አንጓዎቿ ከገባና ብልት ብልትን ከነካ መታጠብ ግዴታ ነው፡፡” (ሙስሊም ዘግበውታል)
በዚህ ሁኔታ ግን ወንድ አስር አመት እድሜ ወይም ሴት ዘጠኝ አመት ካልሞላቸው መታጠብ ግዴታ አይሆንም፡፡
3. ከሀዲ ኢስላምን ከተቀበለ ወይም ከኢስላም ወጥቶ ከተመለሰ፦ ለዚህ ማስረጃው
“ነብዩ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) ቀይስ ኡብን ዓሲም ሲሰልም እንዲታጠብ አዘውት ነበር” (አቡዳውድ ነሳኢይና ቲርሚዚይ ዘግበውታል)
4. የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም ሲያበቃ፦ የአላህ መልክተኛ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) ለዓኢሻ ቢንት አቢ ሁበይሸ እንዲህ ብለዋታል
“የወር አበባሽ ሲመጣ ሰላትን አቁሚ ሲቋረጥ ደግሞ ገላሽን ታጥበሽ ስገጅ” (ቡኻሪና ሙስሊም)
የወሊድ ደም እንደ ወር አበባ እንደሆነ ዑለማዎች ተስማምተውበታል፡፡
5. መሞት፡- ነብዩ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) ልጃቸው ዘይነብ ስትሞት “እጠቧት” ብለዋል” የሀጅ ስነስርዓት በመፈፀም ላይ ሳለ ስለሞተው ግለሰብም “በውሃና በቁርቁራ እጠቡት” ብለዋል የሞተ ሰው የሚታጠበው ሸሪዓዊ ትዕዛዝን ለማክበር ነው እንጂ ሀደሱን ለማስወገድ አይደለም፡፡
ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!

ትምህርት ቁጥር 2

=*=#የገላ_የትጥበት_ስርዓት=*=

ሁለት አይነት አስተጣጠብ አለ፡፡
*አንደኛው “
كيفية استحباب ” (ሱናን የተከተለ የአስተጣጠብ ሁኔታ)
*ሁለተኛው "
كيفية إجزاء"
(በቂ የሆነ የአስተጣጠብ ሁኔታ)
كيفية استحباب
(ሱናን የተከተለ የአስተጣጠብ ሁኔታ)፡-
እጆችን መታጠብ ከዚያ ብልትንና አካባቢው ማጠብ ከዚያ ለሰላት የሚደረገውን ውዱእ ማድረግ ከዚያ ጣትን በፀጉር ውስጥ በማስገባት በመጐንጐን በውሃ ማራስ ከዚያ ራስ ላይ ሶስት ጊዜ ውሃ መርጨት በመጨረሻም የተቀረውን ሰውነት በውሃ ማዳረስ፡፡ ይህ የአስተጣጠብ አይነት ከዓኢሻ በተላለፈው ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ተቀጥሷል፡፡

كيفية إجزاء, 1
(በቂ የሆነ የአስተጣጠብ ሁኔታ) ፡-
ይህ የአስተጣጠብ አይነት በልቡ በማሰብ አካልን ሙሉ በሙሉ በውሃ ማዳረስ ብቻ ነው፡፡ መይሙና ባስተላለፉት ሀዲስ “ነብዩ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) የገላ መታጠቢያ ውሃ አስቀመጡና ከዚያ ውሃ ወደ እጃቸው በማፍሰስ ሁለት ወይም ሶስት ጊዜ ታጠቡ ከዚያ አፋቸውን ተጉመጠመጡ፣ በአፍንጫቸው ውሃ ሳቡና አወጡ፣ ፊታቸውንና እጃቸውን ካጠቡ በኋላ ውሃ በራሳቸው ላይ አፈሰሱ፣ ከዚያ አካላቸውን ታጠቡ፡፡ ሲጨርሱ ፎጣ ባመጣላቸውም እሳቸው ግን አልፈለጉም በእጃቸው ውሃውን ማድረቅ ጀመሩ፡፡”
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

በተመሳሳይ መልኩ ከዓኢሻ በተላለፈው ሀዲስ ላይ “ራሳቸው በውሃ እስኪርስ ድረስ እጃቸውን በማስገባት እየጐነጐኑ አደረሱ ከዚያ ራሳቸው ላይ ሶስት ጊዜ ውሃ ከረጩ በኋላ የተቀረው አካላቸውን አጠቡ፡፡”
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

=*=ሴት ልጅ ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ ገላዋን ስትታጠብ ፀጉሯን በመፍታት አትገደድም፡፡
=*=ከወር አበባ አብቅታ ስትታጠብ ግን መፍታት አለባት፡፡ ለዚህ ማስረጃ ኡሙ ሰለማ ባስተላለፉት ሀዲስ “ለአላህ መልዕክተኛ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) እንዲህ በማለት ጠየቋቸው “እኔ ፀጉሬን ስለምሰራው ለጀናባ ትጥበት መፍታት አለብኝን?” እሳቸውም “አይ ራስሽ ላይ ሶስት ጊዜ ረጭተሽ ከዚያ ላይሽ ላይ ካፈሰስሽ በቂ ነው ትፀጂያለሽ” ብለዋል፡፡
(ሙስሊም ዘግበውታል)


ትምህርት ቁጥር 3

የተወደዱ ትጥበቶች
ገላን መታጠብ የሚያስገድዱ ነገሮችን ከላይ ጠቅሰናል፡፡ ሱና የሆኑ ትጥበቶች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. ከእያንዳንዱ የግብረ ስጋ ግንኙነቶች በኋላ መታጠብ፦ አቡ ራፊዕ ባስተላለፉት ሀዲስ
“አንድ ሌሊት ነብዩ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) አንዷ ሚስታቸው ጋር ተገናኝተው ታጠቡ፡፡ ሌላዋም ጋር ተገናኝተው ታጠቡ
“የአላህ መልዕክተኛ ሆይ አንድ ላይ አንዴ ቢታጠቡስ?” ስላቸው እሳቸውምእንዲህ አሉኝ “ይህ የተሻለ ያማረና ይበልጥ የሚያፀዳ ነው፡፡” (አቡዳውድና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል)
2. ለጁምዓ መታጠብ፦
ነብዩ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) እንዲህ ብለዋል:-
“ወደ ጁምዓ ስትመጡ ታጠቡ” (ቡኻሪ ዘግበውታል)
ይህ ትጥበት ከሁሉም ሱና ትጥበቶች ይበልጥ የፀና ነው፡፡
3. ለሁለቱ ዒዶች መታጠብ
4. ኡምራንና ሀጅ ለማድረግ መታጠብ
ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!

                     ትምህርት ቁጥር 4

            #ገላን_መታጠብ_ግድ_የሆነበት_ሰው_የሚከተሉት_ህግጋቶች


ገላን መታጠብ ግድ የሆነበት ሰው የሚከተሉት ህግጋቶች

1. መስጂድ ለመተላለፍ እንጂ ገብቶ መዘግየት አይፈቀድለትም፦
አላህ እህዲህ ይላል፡-
‹‹መንገድን አላፊዎች ካልኾናችሁ በስተቀር (አካላታችሁን) እስከምትታጠቡ ድረስ ስግደትን አትቅረቡ፡፡›› (አል ኒሳእ 43)
ውዱእ ካደረገ ግን ብዙ ሰሃቦች በነብዩ ዘመን ሲፈፅሙት ስለነበር መስጂድ መቆየት ይፈቀድለታል፡፡ ምክንያቱም ውዱእ አንዱ ጠሃራ በመሆኑ “ሀደሱን” ያቀለዋል፡፡
2. ቁርአንን መንካት አይፈቀድም፦
አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹የተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም፡፡›› (አል ዋቂዓ 79)
ነብዩም (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) እንዲህ ብለዋል
“ቁርአንን ንፁህ እንጂ መንካት የለበትም”
(ማሊክና ሃኪም ዘግበውታል)
3. ጀናባ የሆነ ሰው ከቁርአን ትንሽም ቢሆን ማንበብ የለበትም፦ ዓሊይ ባስተላለፈው ሀዲስ
“ነብዩ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) ጀናባ ካልሆነ በቀር ቁርአንን ከማንበብ የሚያግዳቸው ነገር አልነበረም”
(አህመድ ኢብኑማጃህ ቲርሚዚይ ዘግበውታል)
እንዲሁም ቁርአንን ማንበብ መከልከል ቶሎ እንዲታጠብ የሚገፋፋ ነው፡፡
ከሚከለከላቸው ነገሮች ሌሎች፦
4. ሰላት
5. ካዕባን ጠዋፍ ማድረግ፦ እነዚህን ክፍል አምስት ላይ ውዱእን የሚያስገድዱ ነገሮችን ስንተነትን ገልፀናል፡፡

SHARE THIS POST   

  • Facebook
  • Twitter
  • Myspace
  • Google Buzz
  • Reddit
  • Stumnleupon
  • Delicious
  • Digg
  • Technorati
Author: Mohammad
Mohammad is the founder of STC Network which offers Web Services and Online Business Solutions to clients around the globe. Read More →

0 comments: