Download this Blogger Template by Clicking Here!

Ad 468 X 60

Saturday 23 August 2014

Widgets

ፊቅህን የመማር ጥቅም


ፊቅህን የመማር ጥቅም
www.facebook.com/easyfiqh

ፊቅህን ማወቅና ተግባራዊ ማድረግ የአንድን ግለሰብ መስተካከል፣ የአምልኮው መቃናትንና በጉዞው ላይ ቀጥተኛ መሆንን ያፈራል፡፡ የግለሰብ መስተካከል ደግሞ የማህበረሰብ መስተካከል ነው፡፡ በመሆኑም ውጤቱ በዱንያ የበላይነትና የደላደለ ህይወትን መኖር ሲሆን በአኺራ ደግሞ የአላህን ውዴታና ጀነትን መጐናፀፍ ነው፡፡ ዲንን ገንዘብ ከስራዎች ምርጡና ከአይነቶች ጥሩው ነው፡፡ የቁርአንና የሀዲስ ጥቅሶች ትሩፋቱን ገልፀው በመማር አነሳስተዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱ ይህ የአላህ ቃል ነው፡፡
وما كان المؤمنون لينفروا كافة فلولا نفر من كل فرقة منهم طائفة ليتفقهوا في الدين ولينذروا قومهم إذا رجعوا إليهم لعلهم يحذرون - التوبة: ١٢٢
‹‹
ምእምናንም (ከነቢዩ ጋር ካልኾነ) በሙሉ ሊወጡ አይገባም፡፡ ከእነሱ ውስጥ ከየክፍሉ አንዲት ጭፍራ ለምን አትወጣም፡፡ (ሌሎቹ) ሃይማኖትን እንዲማሩና ወገኖቻቸው ወደነርሱ በተመለሱ ጊዜ እንዲጠነቀቁ ይገስጹዋቸው ዘንድ (ለምን አይቀሩም)፡፡›› (ተውባህ 122)
ነብዩም صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋልአላህ መልካምን ሻለት ሰው ዲንን እንዲገነዘብ ያደርገዋል››
ነብዩ صلى الله عليه وسلم መልካምን ነገር ሁሉ ዲንን ከመገንዘብ ጋር አያይዘውታል፡፡ ይህ የሚጠቁመው ወሳኝነቱንና ከፍተኛ ደጀ ያለው መሆኑን ነው፡፡ በሌላም ሀዲስ ነብዩ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፤ "خياركم في الجاهلية خياركم في الإسلام إذا فقهوا"
በጃሂሊያ ዘመን ምርጥ የነበሩት ኢስላም ውሰጥም ግንዛቤያቸው ካደገና ከተማሩ ምርጦች ናቸው፡፡
ዲንን መገንዘብ ኢስላም ውሰጥ ከፍተኛ ቦታ ያለውና ምንዳውም የላቀ ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ ሙስሊም ዲኑን የሚገነዘብ ከሆነና የሚኖረውንና የሚኖርበትን መብትና ግዴታ ካወቀ ጌታውን በእውቀት በማምለክ ለዱንያና ለአኺራ እድለኝንትን ይጐናፀፋል፡፡ ውድ አንባቢ! በሳምንት ውስጥ ኢስላማዊ እውቀትን ለመቅሰም ምን ያክል ጊዜ ትሰጣለህ?



*********የፊቅህ ትርጉም ና ምንጮች፣ ---------

------------------የፊቅህ ትርጉም----------------
“ፊቅህ” በዓረብኛ ቋንቋ መገንዘብ ማለት ነው፡፡ አላህ ሹዓይብ ህዝቦች ያሉትን ሲናገር እንዲህ ይላል፡-
قَالُوا يَا شُعَيْبُ مَا نَفْقَهُ كَثِيرًا مِّمَّا تَقُولُ
‹‹ከምትለው ነገር ብዙውን አንገነዘብም፡፡››(ሁድ 91)
እንዲህም ብሏል
وَلَٰكِن لَّا تَفْقَهُونَ تَسْبِيحَهُمْ
‹‹ግን ማጥራታቸውን አታውቁትም፡፡››(አል ኢስራእ 44)
ፊቅህ ትምህርታዊ ትርጉሙ፡-
ተግባራዊ የሆኑና ከዝርዝር መረጃዎች የተወሰዱ ሸሪዓዊ ድንጋጌዎችን ማወቅ ማለት ሲሆን አንዳንዴም ህግጋቶች እራሳቸው ፊቅህ ይባላሉ፡፡
ወሳኝ የሆኑ የፊቅህ ምንጮች፦
1. ቁርአን
2. ሀዲስ
3. የዑለማዎች ስምምነት (ኢጅማዕ)
4. ቂያስ




                                 የፊቅህ አርዕስት፦

ፊቅህ በጥቅሉ ሰዎች ከጌታቸው ከራሳቸውና ከማህበረሰባቸው ጋር የሚኖራቸውን የግንኙነት ደንብ ይዳሰሳል፡፡ እንዲሁም ሰዎች የሚናገሩትን፣ የሚሰሩትን፣ የሚዋዋሉትንና የሚለዋወጡትን ነገራት ፍርዳቸውን የሚዳስስ ሲሆን ይህ ድንጋጌ በሁለት ይከፈላል፡፡
አንደኛው አምልኳዊ ድንጋጌ፡- ለምሳሌ ሰላት፣ ፆም፣ ሀጅና የመሳሰሉት ሲሆን
ሁለተኛው ማህበራዊ ግንኙነት፡- ለምሳሌ መዋዋል፣ መለዋወጥ፣ ቅጣቶች፣ ድንበር መተላለፎች፣ ተጠያቂነቶችና ሌሎችም ሰዎች እርስ በርስ የሚኖራቸውን ግንኙነት ስርዓት የሚያስይዙ ነገሮች ናቸው፡፡
እነዚህን ህግጋቶች እንደሚከተለው ጠቅለል ማድረግ ይቻላል፦
1. ቤተሰባዊ ስርዓቶች ከመጀመሪያው ምስረታ እስከ ፍፃሜው፡- በዚህ ርዕስ ስር ጋብቻ፣ ፍቺ፣ የዘር ሀረግ፣ የቤት ወጪ፣ ውርስና የመሳሰሉት ይካተታሉ፡፡
2. ንግድና ኢኮኖሚያዊ ስርዓተ ደንቦች፡- እንደ መሻሻጥ፣ ማከራየትና በጋራ መስራት የመሳሰሉት የልውውጥ ስርዓቶችን ይዳስሳል፡፡
3. የመካሰስና የመፋረድ ስርዓተ ደንቦች፡- ይህ ደግሞ መካሰስ፣የይገባኛል ጥያቄዎች፣ መፋረድና የመሳሰሉትን የመወሰኛና መሻሪያ መንገዶች የሚጠናበት ነው፡፡
4. ፖለቲካዊ ስርዓተ ደንቦች፡- ይህ ደግሞ ኢስላማዊ ሀገር ከሌሎች ጋር እንዲሁም ውስጥ ካሉ ሙስሊሞች ካልሆኑ ህብረተሰቦች ጋር በጦርነትና በሰላም ሂደት የሚኖር ግንኙነት ሲሆን ጂሃዶችንና ስምምነቶችን ያካትታል፡፡

SHARE THIS POST   

  • Facebook
  • Twitter
  • Myspace
  • Google Buzz
  • Reddit
  • Stumnleupon
  • Delicious
  • Digg
  • Technorati
Author: Mohammad
Mohammad is the founder of STC Network which offers Web Services and Online Business Solutions to clients around the globe. Read More →

0 comments: