Download this Blogger Template by Clicking Here!

Ad 468 X 60

Monday 25 August 2014

Widgets

በጫማ ላይ የማበስ ሸሪዓዊ ድንጋጌውና ማስረጃው



ትምህርት 1
 

በሙሉ አህለሱና ወልጀምዓ ስምምነት በጫማ ላይ ማበስ የተፈቀደ ነው፡፡ በጫማ ላይ ማበስ አላህ ከባሮቹ ጣጣን ለማቅለል ሲል ያግራራው ሲሆን ለመፈቀዱም ማስረጃዎቹ ሀዲስና የኡለማዎች ስምምነት (ኢጅማዕ) ናቸው፡፡
ነብዩ እንደተገበሩት እንዳዘዙትና በዚህ ጉዳይ እንዳግራሩ የሚጠቁሙ ሶሂህ ሀዲሶች በብዛት ተዘግበዋል፡፡
ኢማም አህመድ እንዲህ ብለዋል “ጫማ ላይ ማበስ ለመፈቀዱ ልቤ ውስጥ ትንሽም ጥርጣሬ የለም ይህን የሚያስረዱ ከአርባ በላይ ሀዲሶች አሉ፡፡”
ሀሰነል በስሪይ እንዲህ ብለዋል “ነብዩበጫማቸው ላይ እንዳበሱ ሰባ ሰሃባዎች ነግረውኛል፡፡”

ከነዚህ ሀዲሶች፦ ጀሪር ኢብን አብድላህ እንዳስተላለፉት
“የአላህ መልዕክተኛ ተፀዳዱና ውዱእ ሲያደርጉ በጫማቸው ላይ አበሱ፡፡”( ሙስሊም ዘግበውታል)
አዕመሽ ኢብራሂምን ጠቅሰው እንደዘገቡት
“ይህ ሀዲስ ያስደስታቸው ነበር ምክንያቱም ጀሪር የሰለመው የአልማኢዳው (ስለ ውዱእ የሚናገረው) አንቀፅ ከወረደ በኋላ ነበርና”
አንድ ሰው ጉዞ ላይ ሲኾንና ሀገርም ሲኾን በማንኛውም ሁኔታ በጫማ ላይ ማበስ እንደሚችል ሁሉም አህሉ ሱና ወልጀመዓ ተስማምተዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ “በጀውረብ” ላይ ማበስም የተፈቀደ ነው፡፡ “ጀውረብ” ከቆዳ ያልሆነ ማለትም ከጨርቅ ወይም ከሌላ የሚሰራ የእግር ልብስ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ካልሲ ማለት ነው፡፡ ካልሲ ላይ ማበስ የተፈቀደው ልክ እንደጫማ ለእግር አስፈላጊ ስለሆነና የሚታበስበትም ምክንያት ተመሳሳይ ስለሆነ ነው፡፡ ስለዚህ እግርን የሚሸፍን እስከሆነ ድረስ ማበስ ይቻላል፡፡



1. ከውዱእ በኋላ የተለበሱ መሆን አለባቸው፦ ለዚህ ማስረጃው ሙጊራ እንዳሉት
“ከነብዩ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) ጋር ጉዞ ላይ ሳለን ውዱእ አደረጉና ጫማቸውን ለማውለቅ ስንደረደር “ተዋቸው ውዱእ አድርጌ ነው ያጠለቅኳቸው አሉና በላያቸው ላይ አበሱ፡፡”
(“ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

2. እግር መተጠብ እስካለበት ቦታ ድረስ መሸፈን አላባቸው፦ እግር መታጠብ ካለበት ቦታ ውስጥ የተወሰነ ከተገለፀ ማበስ አይፈቀድም፡፡
3. የተፈቀዱ መሆን አለባቸው፦ የተነጠቁ ወይም የተሰረቁ ከሆነ እንዲሁም ደግሞ ወንድ ልጅ ከሀር የተሰራ ካልሲ መልበስ ኃጢአት በመሆኑ ይህን ለበሶ ከሆነ ማበስ አይፈቀድም፡፡
4. ጫማው ከጦሃራ የተሰራ መሆን አለበት፦ ከነጃሳ ቆዳ የተሰራ ከሆነ ማበስ አይፈቀድም፡፡
5. በጫማ ላይ እየታበሰ የሚቆየው በሸሪዓው እስከተገደበው ጊዜ ብቻ መሆነ አለበት፦ እሱም ሀገሩ ላይ ከሆነ አንድ ቀን ከነሌሊቱ ጉዞ ላይ ከሆነ ደግሞ ሶስት ቀናት ከነሌሊታቸው ነው፡፡
እነዚህ አምስቱ መስፈርቶች ዑለማዎች በጫማ ላይ ማበስ የተሳካ እንዲሆን ከነብዩ ሀዲሶችና ከጥቅል ህግጋቶች የወሰዷቸው በመሆናቸው ለማበስ ሲፈለግ እነዝህን ማሟላት ግዴታ ነው፡፡

ትምህርት ቁጥር 3

-----<[#የአስተባበስ_ሁኔታ]>----


መታበስ የተደነገገለት ቦታ የጫማ የላይኛውን ክፍል ሲሆን አብዛኛውን የጫማ ክፍል ማበስ በቂ ነው፡፡ ለዚህ ማስረጃ ሙጊራ ኢብን ሹዕባህ ስለ ነብዩ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) አስተባበስ ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል
“ነብዩ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) የጫማቸውን የላይኛው ክፍል ሲያብሱ አይቻለሁ ብለዋል፡፡”
የጫማን የስረኛው ክፍልና ተረከዝን ማበስ አይፈቀድም ሱናም አይደለም፡፡
ዓሊይ እንዲህ ብሏል
“ዲን የሰዎችን አስተያየት የተከተለ ቢሆን ኖሮ የጫማ ስረኛውን ማበስ ላይኛውን ከማበስ የተሻለ ነበር ነገር ግን ነብዩ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) ያበሱት ላይኛውን ነው፡፡” (አቡዳውድና በይሐቂይ ዘግበውታል)

የጫማን የላይኛውንና የስረኛውን ክፍል አንድ ላይ አድርጐ ማበስ የተጠላ ተግባር ቢሆንም እበሳው ግን ትክክል ነው፡፡
                            ትምህርት ቁጥር 4

                         =====<[#ቀነ_ገደቡ]>===

ጫማን እያበሱ (ሳያወልቁ) መቆየት የሚቻለው ሀገሩ ኗሪ የሆነ ወይም ደግሞ ተጓዥ ሆኖ ጉዞው ሰላትን ለማሳጠር የማይፈቅድለት ከሆነ አንድ ቀን ከነሌሊቱ ሲሆን ጉዞው ሰላትን ለማሳጠር የሚፈቅድለት ተጓዥ ከሆነ ደግሞ ሶስት ቀን ከነሌታቸው መቆየት ይችላል፡፡
ለዚህ ማስረጃ ዓሊይ እንዲህ ብለዋል
“የአላህ መልዕክተኛ የተጓዥን ቀነገደብ ሶስት ቀን ከነሌሊታቸው የሀገር ኗሪን ደግሞ አንድ ቀን ከነሌሊቱ አድርገዋል፡፡”
(ሙስሊም ዘግበውታል)
                            ትምህርት ቁጥር 5

                         =====<[#አፍራሾቹ]>====

ጫማ ላይ ማበስ በሚከተሉተ ነገሮች ሊበላሽ ይችላል፦
1. ገላን መታጠብ የሚያስገድድ ነገር ከተከሰተ ይበላሻል፦ ለዚህ ማሰረጃው ሰፍዋን ኢብን ዓሳል እንዳሉት “ነብዩ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም)
ጉዞ ላይ ስንሆን ጀናባ እስካልሆንን ድረስ ለሶስት ቀናት ከነሌሊታቸው ጫማን እንዳናወልቅ ያዙን ነበር” (አህመድ፣ ነሳኢይና ቲርሚዚይ ዘግበውታል)

2. እግር መታጠብ ካለበት ቦታ የተወሰነው ቢገለፅ እበሳው ይፈርሳል፡፡

3. ጫማዎችን ማውለቅ እበሳን ያፈርሳል፦ የአንዱን እግር ብቻ ማውለቅም እንደ አብዛኞች ዑለሞች አቋም ሁለቱንም እንደማውለቅ ይቆጠራል፡፡

4. የቀነ ገደቡም ማብቃት እበሳን ያፈርሳል፦ ምክንያቱም እየታበሰ መቆየት የሚቻልበትን ቀን ሸሪዓው በመወሰኑ እሱን መተላለፍ አይፈቀድም፡፡

                             ትምህርት ቁጥር 6

                        =<[ቀነ_ገደቡ_የሚጀምርበት_ቀን]>

የእበሳው ቀነ ገደብ አንድ ብሎ የሚጀምረው አንድ ሰው ጫማውን ከለበሰ በኋላ ውዱእን ከሚፈታበት ጊዜ ጀምሮ ነው:: ለምሳሌ አንድ ሰው ለሱብሂ ውዱእ አድርጐ ጫማውን ካጠለቀ በኋላ ፀሐይ ሲወጣ ውዱእ ቢፈርስና ከዚያ ዙህር ወቅት ላይ ውዱእ ቢያደርግ የእበሳው ቀነ ገደብ አንድ ብሎ የሚጀምረው ውዱእ ከፈረሰበት ማለትም ፀሐይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡
አንዳንድ ዑለሞች ግን ቀነ ገደቡ የሚጀምረው ካበሰበት ጊዜ ጀምሮ ነው ይላሉ፡፡ ይህ ማለት ከላይ በተሰጠው ምሳሌ መሰረት ውዱእ ካደረገበት ከዙህር ወቅት ጀምሮ ነው ማለት ነው፡፡

                                  ትምህርት ቁጥር 7

                        በእሽግ፣_በጥምጣምና_በሴቶች_ሻሽ_ላይ_ማበስ

እሽግ ያልነው ስብራትን ለመጠገን በእንጨት በጄሶና በመሳሰሉት ማሸግ ሲሆን እንዲሁም ለቁስል የሚደረጉ እንደፋሻ ወይም ጨርቅ ላይም ማበስ ይቻላል፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ እስከ አስፈላጊ ቦታ ድረስ ብቻ የሚሸፍኑ ከሆኑ ሊታበሱ ይችላሉ፡፡ ከአስፈላጊ ቦታ ዘለው የሄዱ ከሆነ ግን ተጨማሪውን ቦታ ገልጦ ማጠብ የግድ ነው፡፡ በነዚህ ላይ ማበስ ለትንሹም ለትልቁም “ሀደስ” የተፈቀደ ነው፡፡
በእነዚህ ላይ ለማበስ ምንም ቀነ ገደብ የለውም፡፡ ይልቁንስ ህመሙ እስኪድንና እስኪፈታ ድረስ እያበሱ መቆየት ይቻላል፡፡ ለዚህ ማስረጃው በነዚህ ላይ ማበስ ችግር የሚያስገድደው ስለሆነ ነው፡፡ ነገር ግን ለችግር የተፈቀደ ነገር በችግሩ መጠን ልክ ይወሰናል፡፡
ሌላው በጭንቅላት ዙሪያ በሚጠመጠም አማኢም (ጥምጣም) ላይም ማበስ የተፈቀደ ነው፡፡ ለዚህ ማስረጃው
ሙጊራ ኢብን ሹዕባህ ባሰተላለፉት ሀዲስ
“ ነብዩ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) አናታቸው፣ ጥምጣማቸው ላይና ጫማቸው ላይ አብሰዋል፡፡” (ሙስሊም ዘግበውታል)
ጥምጣም ላይ ማበስ ምንም ቀነ ገደብ የለውም ነገር ግን ለጥንቃቄ ሲባል ውዱእ ተደረጐ የተለበሰን ጥምጣም ቢታበስና ለጫማ በተደረገው ቀነ ገደብ መሰረት ቢታበስ የተሻለ ነው፡፡
የሴቶች ሻሽ ግን ማውለቅ የሚያስቸግር ወይም ጭንቅላቷ ላይ በሽታ ካለ በስተቀር አለማበስ የተሻለ ነው፡፡
ጭንቅላት በሂና ወይም በሌላ ነገር የተመረገ ከሆነ ማበስ ይቻላል፡፡ ምክንያቱም ነብዩ ያደርጉት ነበር፡፡ በተጨማሪም ራስን ማበስ ሸሪዓው ለኡማው ያግራራው ነው፡፡

SHARE THIS POST   

  • Facebook
  • Twitter
  • Myspace
  • Google Buzz
  • Reddit
  • Stumnleupon
  • Delicious
  • Digg
  • Technorati
Author: Mohammad
Mohammad is the founder of STC Network which offers Web Services and Online Business Solutions to clients around the globe. Read More →

0 comments: