Download this Blogger Template by Clicking Here!

Ad 468 X 60

Saturday 23 August 2014

Widgets

የተፈጥሮ ግዴታ ፅዳቶች



የተፈጥሮ ግዴታ ፅዳቶች

ይህን ፈፃሚ አላህ ሰዎችን በፈጠረበት ውበት ከመገኘቱ አንፃር ሱነኑል ፊጥራ (ተፈጥሯዊ ሱና) በመባል ይታወቃል::
ይህ ተግባር የተወደደ የሆነበት ምክንያት በሚያምርና በተዋበ ሁኔታ እንዲገኙ ሲባል ነው፡፡
አቡ ሑረይራ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ (
) እንዲህ ብለዋል:-

“ አምስት ነገሮች ተፈጥሯዊ ፅዳቶች ናቸው፡
1የብልትን ፀጉር ማፅዳት፣
መገረዝ፣
ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር፣
የብብትን ፀጉር መንጨትና
ጥፍርን መቁረጥ፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

1. ግርዛት
ለወንድ ግዴታ ሲሆን ለሴት ደግሞ ሱና ነው:: ወንድ መገረዝ ያለበት የወሸላው ሽፋን ከሚይዘው ነጃሳ ለመፅዳት ሲሆን ሴት ደግሞ የስሜቷን ግለት ስለሚያበርድ ነው፡፡
ህፃን በተወለደ በሰባተኛው ቀን ቢገረዝ ቶሎ ለመዳንና በተሟላ ሁኔታ ለማደግ ስለሚረዳው የተወደደ ነው፡፡
2. ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር፡
የውበት፣ የንፅህናና ከሃዲያንን የመለየት መገለጫ በመሆኑ የተወደደ ተግባር ነው፡፡ ቀድሞ ቀመስን እንዲያጥርና ፂምን እንዲቀቅ እንክብካቤ እንዲቸረው የሚያነሳሱ ብዙ ሀዲሶች ተዘግበዋል፡፡
ፂምን መልቀቅና መንከባከብ የውበትና የወንድነት መገለጫ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ብዙ ቀድሞ ቀመስን በማሳደግና ፂምን በመላጭ ወይም በማሳጠር ይህን ነቢያዊ ትዕዛዝ ሲቃረኑ ይስተዋላል:: ይህ ተግባር የነብዩን መመሪያና ትዕዛዛቸውን መጣስ በመሆኑ ጥንቃቄ ያሸዋል::
በዚህ ርዕስ ከተዘገቡ ሀዲሶች ውስጥ አቡ ሑረይራ ከነቢዩ ያስተላለፉት ሀዲስ ይጠቀሳል፡-
“ቀድሞ ቀመስን አሳጥሩ ፂማችሁን ደግሞ ልቀቁ መጁሶችን ተቃረኑ” (ሙስሊም ዘግበውታል)

ማንኛውም ሙስሊም ይህን የነብዩ (
) መመሪያ አጥብቆ በመያዝ ኢ-ኢስላምን መለየትና ሴትንም አለመመሳሰል ይገባዋል፡፡

3. ጥፍርን መቁረጥ፡-
የውበት መገለጫና ቆሻሻንም ማስወገጃ ሲሆን ነገር ግን አንዳንድ ሙስሊሞች ይህን የነብዩ (
) መመሪያ በመቃረን ጥፍራቸውን ወይም ደግሞ የተወሰነ ጣት ጥፍርን በማሳደግ ይህን ነቢያዊ መመሪያ ይቃረናሉ:: ይህ ተግባር የሸይጧን ማታለያና የአላህን ጠላቶች በጭፍን መከተል ነው፡፡

4. የብብትን ፀጉር መንጨት ወይም በመላጨት ማፅዳት፡-
በመጠራቀሙ ምክንያት የሚፈጠረውን ጠረን ያስወግዳል፡፡ ይህ የጠራ ዲናችን ይህን በመሰለ ውበትና ፅዳት የሚያዘን ሙስሊሞች በመልካም ሁኔታ እንዲገኙና በዲናቸው የበላይነት ተሰምቷቸው ከሀዲያንና መሃይማንን እንዲርቁ እንዲሁም አላህን በመታዘዝና የነብዩን መመሪያ በመከተል አላህን እንዲያመልኩ ነው፡፡
 


ከነዚህም ሌላ ተጨማሪ አምስት ተፈጥሯዊ ፅዳቶች አሉ፡፡ እነሱም
==>መፋቂያን መጠቀም፣
==>በአፍንጫ ውሃን መሳብ፣
==>መጉጥመጥ፣
==>የጣቶች መገጣጠሚያዎችን ማጠብና
==>ኢስቲንጃእ ናቸው፡፡
ለነዚህ ማስረጃ ዓኢሻ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል
“አስሩ ተፈጥሯዊ ፅዳቶች ናቸው፡፡
ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር፣
ፂምን መልቀቅ፣
ጥርስን መፋቅ፣
በአፋንጫ ውሃን መሳብ፣
ጥፍሮችን መቁረጥ፣
የጣቶች መገጣጠሚያዎችን ማጠብ፣
የብብትን ፀጉር መንጨት
የብልትን ፀጉር መላጨትና
ኢስቲንጃእ ማድረግ፡፡”
ይህን ሀዲስ ከዘገቡት ውስጥ አንዱ የሆነው ሙስዓብ ኢብኑ ሸይባህ እንዲህ አሉ:-
“አስረኛውን ረሳሁት ግን
መጉመጥመጥ ይመስለለኛል” (ሙስሊም ዘግበውታል)

አልሀምዱሊላህ!!! እስልምናን ለሰጠን ሙስሊም ላደረገን ጌታ!!! ለእያንዳንዳንዱ የሕይወታችን ክፍል ግልጽ እና የማያወላዳ መስመረን ለዘረጋልን ሀያሉ አምላክ ይሁን ::



SHARE THIS POST   

  • Facebook
  • Twitter
  • Myspace
  • Google Buzz
  • Reddit
  • Stumnleupon
  • Delicious
  • Digg
  • Technorati
Author: Mohammad
Mohammad is the founder of STC Network which offers Web Services and Online Business Solutions to clients around the globe. Read More →

0 comments: