Download this Blogger Template by Clicking Here!

Ad 468 X 60

Saturday 23 August 2014

Widgets

መፋቂያ



                                           መፋቂያ

                                     የመፋቂያ ሸሪዓዊ ድንጋጌ

መፋቂያ መጠቀም በየትኛውም ወቅት ሱና (የተወደደ) ነው፡፡ ፆመኛም ጠዋትም ይሁን ከቀትር በኋላ ጥርሱን ቢፍቅ ችግር የለውም፡፡ ምክንያቱም ነብዩ ጥርስን በመፋቅ ሲያነሳሱ አንዱን ወቅት ከሌላው አልለዩም፡፡ ነብዩ (
) እንዲህ ብለዋል:-
“መፋቂያ አፍን የሚያፀዳና አላህንም የሚያስወድድ ነው፡፡”(ቡኻሪ ዘግበውታል)

እንዲህም ብለዋል:-

“ለህዝቦቼ ማስቸገር ባይሆንብኝ ለእያንዳንዱ ሰላት መፋቂያ እንዲጠቀሙ አዛቸው ነበር፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

ይበልጥ የሚወደድበት ወቅት
መፋቂያን መጠቀም በተለይ በነዚህ ወቅቶች ላይ ይበልጥ የተወደደ ነው፡፡
ውዱእ በሚደረግበት ጊዜ፣
ከእንቅልፍ ሲነቃ፣
የአፍ ጠረን ሲለወጥ፣
ቁርአን ለመቅራት ሲባል፣
ሰላት ለመስገድ፣
መስጂድ ሲገባና
ቤት ሲገባ፡፡

ለዚህ ማስረጃው ሚቅዳም ኢብኑ ሹረይህ እንዳስተላለፈው አባቱ ነብዩ (
) ቤት ሲገቡ በምን እንደሚጀምሩ ዓኢሻን ጠይቋቸው ሲመልሱ “ጥርሳቸውን በመፋቅ፡፡” ብለዋል:: (ሙስሊም ዘግበውታል)

ለረዥም ሰዓት በዝምታ ሲቆይና ጥርስ ሲበልዝም ይበልጥ ይወደዳል፡፡

“ነብዩ(
) ሌሊት ሲነሱ አፋቸውን በመፋቂያ ያፀዱ ነበር”(ሙስሊም ዘግበውታል)

በጌታው አምልኮ ሲሆንና ወደርሱ ሲቃረብ በፀዳና ባማረ ሁኔታ መገኘት ይጠበቅበታል፡፡

አላህ በትምህርቱ የምንጠቀምና እየተረሳ ያለውን የጠበቀ የነብዩ (
) ሱናህ የምንተገብር ያድርገን !!!
አምባቢ ብቻ ሳይሆን ተሳታፊም ይሆኑ ዘንድ መፋቂያ (ሲዋክ) መጠቀም ከሚወደድባቸው ወቅቶች መካከል comment ላይ ቢያንስ አንዱን ይጥቀሱ::
ዓላማችን የፊቅህ ትምህርትን ቀለል ባለ አቀራረብ ማስተማር ነው::

                                2 ጥሩ የመፋቂያ አይነት

እርጥብ የማይፈታተልና የማያቆስል እንጨት ቢሆን ይመረጣል፡፡
“ነብዩ በአራክ እንጨት ይፍቁ ነበር፡፡”
መፋቂያውን በቀኝም ይሁን በግራ እጁ ይዞ መፋቅ ችግር የለውም፡፡ ውዱእ በሚያደርግ ሰዓት መፋቂያ ከሌለው ዓሊይ ስለነብዩ ውዱእ አደራረግ በዘገቡት መልኩ በጣት መፋቅ ይቻላል፡፡

የመፋቂያ ጥቅሞች

ከወሳኝ ጥቅሞቹ ውስጥ ከላይ ባሳለፍነው ሀዲስ የተጠቀሰው ለአፍ ፅዳትና አላህንም ማስወደጃ መሆኑ ነው፡፡ ነብዩ (
) እንዲህ ብለዋል:-
“መፋቂያ አፍን የሚያፀዳና አላህንም የሚያስወድድ ነው፡፡”(ቡኻሪ ዘግበውታል)

ስለዚህ ጥቅሙ የላቀ በመሆኑ አንድ ሙስሊም ግለሰብ ይህን ሱና ቸል ሳይል ሊከታተለው ይገባል፡፡
አንዳንድ ሙስሊሞች ወር ሁለት ወር የሚያህል ረዥም ጊዜ ባለማወቅ ወይም በቸልተኝነት ጥርሳቸውን ሳይፍቁ የሚቆዩበት ሁኔታ አለ፡፡ እንደዚህ አይነቱ ሰው ነብዩ (
) የሚንከባከቡትን ሱና በመተዉ ከፍተኛ ምንዳና ብዙ ጥቅሞች ያመልጠዋል፡፡
ነብዩ ህዝቦችን ማስቸገር ይሆንብኛል ብለው እንጂ በግዴታ መልክ ሊያዙት ነበር፡፡ መፋቂያ ከላይ ከተገለፁ ጥቅሞች ውጭም ብዙ ተነግሮለታል፡፡ ከነዚህም ውስጥ
ጥርስንና ድድን ማጠናከሩ፣
ድምፅን ማጥራቱና
ሰውዬውን ማነቃቃቱ ይጠቀሳሉ፡፡
አላህ የነብዩ (
) ሱናህ በአግባቡ መከተልን እንዲያገራልን እንለምነዋለን !!!

SHARE THIS POST   

  • Facebook
  • Twitter
  • Myspace
  • Google Buzz
  • Reddit
  • Stumnleupon
  • Delicious
  • Digg
  • Technorati
Author: Mohammad
Mohammad is the founder of STC Network which offers Web Services and Online Business Solutions to clients around the globe. Read More →

0 comments: